ቦኒ ትንሹ ቱሪስት

 

ይህ “ቦኒ ትንሹ ቱሪስት” መጽሐፍ 2 የተዘጋጀው ዕድሜያቸው ከ6 እስከ 9 ዓመት ለሆኑ ወይም ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ለሚማሩ ህጻናት ተማሪዎች ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም ለህጻናቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሓውልቶችን ማስታዋወቅ ነው።

መጽሐፉ በግል አጥር ጊቢ ይዞታ የሚገኙ ሐውልቶችን አያካትትም። መጽሐፍ 2 የነገሥታት እና የታዋቂ ሰዎች መታሰቢያ ሐውልቶችን የሚያስተዋውቅ ሲሆን መጽሐፍ 1 ደግሞ የሰማዕታት እና የነፃንት ሐወልቶችን የያዘ ነው።

መጽሐፉ የተዘጋጀው ሥዕላዊ በሆነ አቀራረብ ሆኖ፣ ሐወልቶቹ የት የት እንደሚገኙ፣ መቼ እንደተመረቁ፣ ምን ያሀል እንደሚረዝሙ፣ በማን ዲዛይን እንደተደረጉ እና ለምን እንደተሠሩ በሚመልስ መልኩ ነው። እንዲሁም መጽሐፉ በየምዕራፉ የተማሪዎቹን መረዳት የሚለኩ ጥያቄዎችን አካቷል።

 

a, .uk-link { color: #c66322; text-decoration: none; cursor: pointer; }